ምን አይነት መረጃ ነው ምናዘጋጀው?
አንድ ታካሚ በ‘Max Access Solution(MAS)’ ፕሮግራም ሲሳተፍ ከዚህ በታች ያሉትን የግል መረጃዎን እንሰበስባለን፣ እናስቀምጣለን፣ እና እናደራጃለን (በአንድ ላይ ‘እናጠናቅራቸዋለን’)፦
- ስምዎ፡
- ጾታዎ፡
- የትውልድ ቀንዎ፡
- የሚገኙበት ስልክ ቁጥር(ሮች)፡
- የኢሜይል አድራሻዎ፤
- የደብዳቤ አድራሻዎ፤
- ህክምናየሚያገኙበትሆስፒታልእናሃኪምዎ፤
- ገቢዎ ወይም የፋይናንስ ሁኔታዎ (ካሎት ብቻ) እና በመጨረሻም
- የሚንከባከብዎ ሰው የሚገኝበት ዝርዝር አድራሻ (ካሎት ብቻ) ።
(ከላይ የተጠቀሱት በአንድነት የእርስዎ “የግል መረጃ” ሆኑ ማለት ነው፡፡)
ለርስዎ በቂ ድጋፍ እና እንክብካቤ እንድናቀርብ ከዚህ በታች ያሉትን የርስዎን ሚስጥራዊ የሆኑ የግል መረጃዎችን ሰብስበን እናደራጃለን፦
- ምርመራዎን፡
- የተመረመሩበትን ቀን፡
- እያገኙ ያሉትን ህክምና፡
- የ’PCR’ ምርመራ ያደረጉበትን ቀን እና ውጤቶችዎን (ተፈጻሚ ከሆነ)።
(ከላይ የተጠቀሱት በአንድነት የእርስዎ “የግል ሚስጥራዊ የግል መረጃ” ናቸው ማለት ነው፡፡)
የርስዎን ግላዊ መረጃና የግል ሚስጥራዊ መረጃ የግል መረጃዎን የምናደራጀው ለምን እና እንዴት ነው?
በአንዱ የ’MAS’ ፕሮግራማችን እንደ ታካሚ ለመሳተፍ ሲያመለክቱ የግል መረጃዎትን እና ሚስጥራዊ የግል መረጃዎን በቀጥታ ከእርስዎ፣ ከተንከባካቢዎ እና(ወይም) ከሃኪምዎእንሰበስባለን።የግልመረጃዎንእናሚስጥራዊየግልመረጃዎንለሚከተሉትአላማዎችእንጥቀምበታለን፦
- እርስዎን ለመለየት፡
- ከእርስዎ ጋር ለመገናኘት፡
- ለታካሚ ድጋፍ እና እንክብካቤ ለማቅረብ፡
- ስለበሽታዎ ወይም ህክምናዎ በተመለከተ ለእርስዎ መረጃ ለመስጠት፡
- በማንኛውም ህግ ወይም ደንብ መሰረት ያሉብንን ግዴታዎች መወጣት እንዲያስችለን፡
- የፕሮግራሙአስተዳደርንእናበሚሰጠውአገልግሎትዙሪያለሚመለከቱሌሎችማናቸውምአይነትአላማዎች።
(ከላይ የተጠቀሱት በአንድነት የእርስዎን የግል መረጃ እና ሚስጥራዊ መረጃዎትን የምንጠቀምበት “ዓላማዎቹ” ናቸው) ።
የእርሶን መረጃ በማይለይ እና በማይታወቅ መልኩ ለህትመት ልንጠቀምበት እንችላለን። ይህም ማለት እርስዎን የሚለይ ማንኛውም አይነት መረጃ (ለምሳሌ፦ ስምዎ፣ የትውልድ ቀንዎ፣ አድራሻዎ) ይጠፋል፤ስለዚህማንምሰውመረጃዉንከእርስዎጋርአያገናኝምማለትነው።
የርስዎን የግል መረጃ እና ሚስጥራዊ የግል መረጃ ለማን ይፋ እናደርጋለን?
የርስዎን የግል መረጃ እና(ወይም) ሚስጥራዊ የግል መረጃዎትን ይፋ የምናደርገው፦
- በማክስ ፋውንዴሽን ውስጥ ላሉ አካላት እና
- ምናልባት በህግ ከተገደድን ለህግ አስከባሪ ድርጅት ወይም ለመንግስት ድርጅት ይሆናል።
በተጨማሪም የርስዎ የግል መረጃ እና ሚስጥራዊ የግል መረጃዎ በዩናይትድ ስቴትስ በሚዘጋጅ ደህንነቱ በተጠበቀ እና መሰረቱን ድረ–ገጽ ላይ ባደረገ የመረጃ ቋት ላይ ይቀመጣል።
ያለእርስዎ ፈቃድ የግል መረጃዎትን ወይም ሚስጥራዊ የግል መረጃዎትን ለሌላ ሶስተኛ ወገን ይፋ አናደርግም። እንዲሁም የግል መረጃዎ እና(ወይም) ሚስጥራዊ የግል መረጃዎ በአስተማማኝ መልኩ መቀመጡን ለማረጋገጥ ጥበቃ ያደርጋል።
በዚህ ማስታወቂያ መሰረት እርስዎ የግል መረጃዎትን እና ሚስጥራዊ የግል መረጃዎትን እንዳንጠቀም ፈቃደኛ ባይሆኑ ምን ሊከሰት ይችላል?
በዚህ የግል መረጃ ማስታወቂያ መሰረት እርስዎ የግል መረጃዎትን ወይም ሚስጥራዊ የግል መረጃዎትን እንድንጠቀም ፈቃደኛ ባይሆኑ፣ በማክስ ፋውንዴሽን ፕሮግራም ውስጥ ተሳታፊ ላይሆኑ ይችላሉ።
የርስዎ የመረጃ ጥበቃ መብቶችዎ፦
በመረጃ ጥበቃ ህግ መሰረት፣ እርስዎ የሚከተሉትን ጨምሮ መብቶች አልዎት፦
- የማወቅ መብት – የትኛው መረጃዎ እንደተሰበሰበ፣ እንዴት ጥቅም ላይ እየዋለ እንደሆነ፣ ለምን ያህል ጊዜ እንደሚያዝ እና ለሌሎች ሶስተኛ ወገኖች መተላለፍ አለመተላለፉን የማወቅ መብት አልዎት።
- የተደራሽነት መብትዎ – የግልመረጃዎንግልባጭየመጠየቅመብትአልዎት።
- የማረም መብትዎ – ትክክለኛ ያልሆነ ወይም ያልተሟላ የመሰሎትን መረጃዎትን እንድናርም (እንድናስተካክል) የመጠየቅ መብት አልዎት።
- የመሰረዝ መብትዎ – በተወሰኑሁኔታዎችየግልመረጃዎንእንድንሰርዝየመጠየቅመብትአለዎት።
- መረጃዎ አገልግሎት ላይ እንዳውል የመገደብ መብትዎ – በተወሰኑሁኔታዎችየግልመረጃዎአገልግሎትላይእንዳይውልናእንድንገድብእኛንየመጠየቅመብትአልዎት።
- የርስዎ መረጃ አገልግሎት ላይ እንዳይውል የመቃወም መብትዎ – በተወሰኑ ሁኔታዎች የግል መረጃዎ አገልግሎት ላይ እንዳይውል የመቃወም መብት አልዎት።
- የመረጃ ተንቀሳቃሽነት መብትዎ – የሰጡንን መረጃ በተወሰኑ ሁኔታዎች ወደ ሌላ ድርጅት ወይም ለእርስዎ አስተላልፈን እንደሆነ የመጠየቅ መብት አልዎት።
- የህግ ጥሰት ሲኖር መረጃ የማግኘት መብትዎ –
በማንኛውም በግል የጤና መረጃዎት ላይ ደህንነቱ ያልተጠበቀ የህግ ጥሰት ቢፈጠር የማወቅመብትአለዎት።
መብቶችዎን ለመጠቀም ምንም አይነት ክፍያ እንዲከፍሉ አይጠየቁም። ጥያቄ ካቀረቡ ለእርስዎ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ምላሽ እንሰጣለን።
ጥያቄ ለማቅረብ ከፈለጉ፣ እባክዎ በሚከተለው አድራሻ ያግኙን፦
The Max Foundation
1448 NW Market St.
Suite 500
Seattle, WA 98107
+1 (206) 778-8660
info@themaxfoundation.org